ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት ( የመጨረሻ አስተያየት)
በመጀመሪያ ጊዜህን ሰጥተህ የጠየኩትን መረጃ ስለሰጠኸኝ ምሥጋናዬ ይድረስህ። በተደጋጋሚ እንደገጵኩት የአንተን የድምጵ መልእክት የሰማሁት ማስታወሻውን ከመጻፌ በፊት በማህበራዊ ድረገጾች በሰፊው እየተራገበ በመመልከቴ ነው። አንተ እኔን ለመወረፍ እንደሞከርከው ” ጊዜና ሁኔታ ያላገናዘበ” ሳይሆን አጀንዳውን ጐትተው ወደ መድረክ ያመጡት ወቅታዊ በመሆኑ ነው።
ከአንዳንድ ወዳጆቼ ጋር በነበረን ምልልስ እንደገለፅኩት ይህን ሰነድ ወደ ፊት ይዞ መምጣት አሁን የሚደረገውን የኢትየጵያ ሙስሊሞች የነፃነት ትግል ጥላሸት ለመቀባትና ለመቀልበስ በማሰብ ነው። ባጭሩ ያቀረብከው ሰነድ መቼም ይሁን መቼ ” ጊዜውን እየጠበቀ የሚፈነዳ ፈንጂ” መሆኑን አስምሬበታለሁ። አሁንም እምነቴ ይህ ነው።
በዝርዝር ካነሳሀቸው ጉዳዬች አንዳንዶቹን ነቅሼ በማውጣት ነጥብ በነጥብ አስተያየት ልስጥበት፣
Category: ትንታኔ
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ለአቶ ኤርሚያስ ለገሰ የሰጠው ምላሽ
“ቢሮህ አስጠርተህን ቤተ ክርስቲያኒቱንና የፈረደበትን አማራ ምን ብለህ እንደተሳደብክ የምናውቀው አንተ እና እኛ ነን፡፡”ኤርምያስ ኤርምያስ ሆይ!የኤርምያስ ለገሠን ‹ግልጽ ደብዳቤ› አነበብኩት፡፡ አንብቤው በሁለት ምክንያት ሳልጽፍለት ዘገየሁ፡፡ በአንድ በኩል ስለ ኤርምያስ ከነበረኝ የዋሕ ግምት የተነሣ ኤርምያስን ያህል ሰው ይህን ያህል አይሳሳትምና በቀጣዮቹ ቀናት በስሜ የወጣ ጽሑፍ ነው እንጂ የጻፍኩት እኔ አይደለሁም ይል ይሆናል ብዬ በመገመት፡፡ጽሑፉ እንደወጣ ብዙ ሰዎች አሁን እኔ የምነግርህን ሲገልጡት ነበርና ትሰማቸዋለህ ብዬ አስቤ ነበር፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሐዲስ ዓለማየሁ የባሕል ማዕከል ባዘጋጀው ዐውደ ጥናት ላይ ልካፈል ወደ ደብረ ማርቆስ ተጉዤ ስነበር፡፡
ማስተርስ/ዶክተሬት እንደ መለዋወጫ እቃ!
ታሪኩ አባዳማ | የካቲት 2007 ልጄ አስራ ሁለተኛ ክፍል ስለጨረሰ የደስታዬ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ… የሚል ግብዣ ደርሷችሁ አያውቅም? እናንተም ፋሽኮ ቪኖ ወይንም እናትና ልጅ አረቄ ይዛችሁ ድግሱን ለማድመቅ ሳትሄዱ አልቀራችሁም – የዚያን ዕለት ጎረምሶቹ የቀለጠ ፓርቲ ደግሰው እስኪነጋ ይጨፍራሉ አሉ… ይህስ ይሁን።እንድህረ ምረቃ ፕሮግራም ላይ መሆኑን አንድም ቀን ሲናገር ሰምታችሁ የማታውቁት በቅርብ የምታውቁት ሰው ፣እንዲያውም በመደበኛ ትምህርት ከስንተኛ ክፍል ነበር? አቋርጦ ወደ ሄደበት ሄዶ (ጫካ ወይንም ምርኮ) ግን የዛሬ ‘ሹም’ ‘የማስተርስ ፣ ዶክትሬት ዲግሬዬ በፖሰታ ስለደረሰኝ የደስታዬ ተካፋይ እንድትሆን ብሎ ቢጠራችሁስ? ይኼ ሰው ድሮ ትምህርት ቤት የተመዘገበበት ስም ሌላ ነበር… አሁን ደግሞ አዲስ ስም ብቻ ሳይሆን አዲስ ማዕረግ ፣ አዲስ ቤት ፣ አዲስ መኪና… ምኑ ቅጡ… ባናቱ ላይ ዲግሪ ሸምቶበታል።
ኢሳያስ አፈወርቂን በጨረፍታ
ኢሳያስ አፈወርቂን በጨረፍታ ክንፉ አሰፋ “አንድም ቀን ስቀን አናውቅም!” አሉ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም። ይህን በሚሉ ጊዜ እፊታቸው ላይ ፈገግታ ይታይ ነበር -ምሬቱ እንዳለ ሆኖ። ኢሳያስ አፈወርቂ ሲስቁ አይተናቸው አናውቅም። ግን ኮስተር ብለው የሚናገሩት ነገር እኛኑ አያሳቀን ነው። “ካሳ ይገባናል! ካሳ ስጡን” ሲሉ አሳቁን። ቀጠል አድርገውም “ምጽዋና አሰብን ወያኔ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲጠቀምበት ፈልገው” እንደነበር ተናግረው አሳቁን። “…የሰራነው ጥፋት ስለሌለ የሚጸጥተን ነገር የለም።” አሉ እጃቸውን እንደ ጲላጦስ እያጠቡ። ከዚህ ቀደም ለስዊድኑ ጋዜጠኛ የአስመራው የፖለቲካ ስርዓት ስዊድን ካለው ስርዓት የተሻለ እንደሆነ አስረግጠው ነገሩት።