ኢሳያስ አፈወርቂን በጨረፍታ

isaayasኢሳያስ አፈወርቂን በጨረፍታ ክንፉ አሰፋ “አንድም ቀን ስቀን አናውቅም!” አሉ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም። ይህን በሚሉ ጊዜ እፊታቸው ላይ ፈገግታ ይታይ ነበር -ምሬቱ እንዳለ ሆኖ። ኢሳያስ አፈወርቂ ሲስቁ አይተናቸው አናውቅም። ግን ኮስተር ብለው የሚናገሩት ነገር እኛኑ አያሳቀን ነው። “ካሳ ይገባናል! ካሳ ስጡን” ሲሉ አሳቁን። ቀጠል አድርገውም “ምጽዋና አሰብን ወያኔ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲጠቀምበት ፈልገው” እንደነበር ተናግረው አሳቁን። “…የሰራነው ጥፋት ስለሌለ የሚጸጥተን ነገር የለም።” አሉ እጃቸውን እንደ ጲላጦስ እያጠቡ። ከዚህ ቀደም ለስዊድኑ ጋዜጠኛ የአስመራው የፖለቲካ ስርዓት ስዊድን ካለው ስርዓት የተሻለ እንደሆነ አስረግጠው ነገሩት።